});

34 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ባለሀብቶችና ደላሎች በቁጥጥር ስር ዋሉ::


ሰበር ዜና 34 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ባለሀብቶችና ደላሎች በቁጥጥር ስር ዋሉ:: በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 34 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ባለሀብቶችና ደላሎች በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢፌዲሪ መንግስት ኮ/ጉ/ፅ/ቤት አስታወቀ:: የኢፌዲሪ መንግስት ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ 34 የሚሆኑ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ባለሀበቶችና ደላሎች በቁጥጥር ስር የዋሉት የመንግስትና የህዝብ ሀብትን በሙስና በመመዝበራቸው ነው:: በፖሊስ ዐቃቢ ህግና በፌደራልና አዲስ አበባ ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች በተደረገ የማጣራት ስራ የሙስና ተግባር ውስጥ ተሳትፈው የተገኙት 34 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉት መንግስት ሙስናን ለመከላከል በያዘው ቁርጠኛ አቋም ነው ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል:: ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 34 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ተነግሯል፡፡ ሙሰኞችን የመያዝና በህግ ተጠያቂ የማድረጉ ስራ የሚቀጥል ነው ያሉት ዶ/ር ነገሪ፤ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመቆም መረጃ የመስጠትና የሙስና ተግባር ውስጥ የተሳተፉትን በማጋለጥ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል:: በሙስና ወንጀል ተሳትፈው በቁጥጥር ስር የዋሉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የተገኙባቸው የመንግስት ተቋማት ጥቂቶቹ - የፌደራል መንገዶች ባለስልጣን - የአዲስአበባ መንገዶች ባለስልጣን - ስኳር ኮርፖሬሽን - የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሲሆኑ ሙሰኞችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ ቀጣይነት ያለው በመሆኑ የተቋማትና አሁን የተያዙትን ጨምሮ በቀጣይም በቁጥጥር ስር የሚውሉ ግለሰቦች ማንነትና የተሳተፉበት የወንጀል ዝርዝር በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ሲሉ ሚኒስትሩ ጨምረው ተናግረዋል