});

መሬት የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ንብረት?


ታሪካችን እንደሚያሳየን የመሬት ነገር ከግለሰብ መብትም ያለፈ አንድምታ አለው፡፡ ሕገ መንግሥቱ መሬትን በተመለከተ በአንቀጽ 40(3) ላይ የሚከተለው ተደንግጎ እናገኛለን፡፡ “የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግሥትና የሕዝብ ብቻ ነው፡፡ መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው፤” ይላል፡፡ በአንቀጽ 51(5) ደግሞ የፌዴራል መንግሥት “የመሬት የተፈጥሮ ሀብትና የታሪክ ቅርሶች አጠቃቀምና ጥበቃን በተመለከተ ሕግ ያወጣል፤” ይላል፡፡ በአንቀጽ 89(5) ደግሞ “መንግሥት መሬትና የተፈጥሮ ሀብትን በሕዝብ ስም በይዞታው ሥር በማድረግ ለሕዝቡ የጋራ ጥቅምና ዕድገት እንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፤” ይላል፡፡ በመሆኑም የመሬትና የብሔሮች ግንኙነት ከፍተኛ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ ይህ እንግዲህ ማንነትን ከሚመለከተው ጉዳይ ውጭ ነው፡፡

የብሔሮች የራስን ዕድል በራስ መወሰን መብትም ቢሆን ኢኮኖሚያዊ ዘርፍም አለው፡፡ ፖለቲካዊው ብቻውን ዳቦ አይሆንም፡፡ ፖለቲካዊ ነፃነት በኢኮኖሚያዊ ነፃነት መታገዝ አለበት፡፡ ለዚያም ነው በአንድ ወቅት የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጁሌስ ኔሬሬ፣ አሩሻ ላይ የካቲት እ.ኤ.አ. 1979 “አፍሪካውያን መጻኢ ዕድላችንን የመወሰን ነፃነት እንደሌለን፣ በኢኮኖሚ ገና ከጥገኝነት እንዳልወጣን፣ በከፊልም ገና ከቅኝ ግዛት ያልተላቀቅንና ሉዓላዊ ነን ብለን አፋችንን ሞልተን መናገር አንችልም፤” በማለት ምሬት በተሞላበት አኳኋን የገለጹት፡፡

ከላይ የቀረበው ሐሳብ ለክልሎችም በትክክል ይሠራል፡፡ በኢኮኖሚ ራሳቸውን የማይችሉ ክልሎች ከሆኑ ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብታቸው ውኃ እንደሚበላው ሃቅ ነው፡፡ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕቅዶችን ለማቀድም ሆነ ለማከናወንም በኢኮኖሚ ራስን መቻል ተቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ በፌደራሉ መንግሥት ላይ ጥገኛ ሆኖ በሙሉ ነፃነት ራስን ማስተዳደር የሚቻልም አይደለም፤ የሚታሰብም አይሆንም፡፡

በኢትዮፒያ በለፉት 27 አመታት እንደ ሀገር ሁሉም በእኩል የተጠቃሚነት ጉዳይ ስናነሳ `` አደባባይ ያወቀው ጸሃይ.....`` እንደሚባል አይነት ነጋር ነው ።አንድ ምሳሌ ማንሳቱ ብቻ በቂ ነው።የትግራይ ተወላጅ ከ2005-2009 ዓም በኢንቨትመንት ስም የጋምቤላ ክልል መሬትን በመቀራመት ቀዳሚ ስፍራ ላይ ነበሩ።በዚህም ሳያበቃ መሬቱን መልሰው በማስያዝ ከኢትዩጵያ ልማት ባንክ 2,460,457,327.15(ሁለት ቢልዩን አራት መቶ ስልሳ ሚልዩን አራት መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ሀያ ሳባት ብር ከ15 ሳንቲም) በብድር ስም የወሰዱ ሲሆን፣ ከብድሩ ውስጥ 99% አልተመለሰም። መሬቱም ለታሰበለት አላማ አልዋለም።ግለሰቦቹ ወስደው ካጠናቀቁ በኋላም ባንኩ ማበደር እንዲያቆም ተደርጓል!!

የራስን ዕድል በራስ መወሰን ኢኮኖሚያዊ ገጽታው የመልማት መብትና የተፈጥሮ ሀብትን በነፃነት ለሚፈልጉት አገልግሎት ማዋልን ይይዛል፡፡ ከቅኝ ግዛት ነፃ ሲሆንም በተገዥዎች ላይ ተፈጽሞ የነበረው አንዱ ኢፍትሐዊ ድርጊት የተፈጥሮ ሀብትን መበዝበዝ ስለነበር፤ ይህ የብዝበዛ አድራጎት በድጋሜ እንዳይከሰት፣ ይልቁንም በተፈጥሮ ሀብታቸው የመጠቀም መብትን ማረጋገጥ ነበር፡፡በኢኮኖሚ የመበልፀግና የመልማት መብትና የተፈጥሮ ሀብትን ያላንዳች ጫናና ጣልቃ ገብነት መጠቀምን በተመለከተ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ጀምሮ፣ በየአኅጉራቱና በየአገሮቹ ብዙ ሕጎች አሉ፡፡ የሁሉም ይዘት ተመሳሳይና ተቀራራቢ ነው፡፡ በቅኝ ግዛትና በወረራ የሌሎች ሕዝቦችን የተፈጥሮ ሀብት መበዝበዝን ዓለማቀፍ ሕጉ ይከለክላል፡፡ የማይዳፈሩት፣ የማይናወጥና የማይቀየር አንዱ የሉዓላዊነት መገለጫም ጭምር ነው፡፡ ልማት፣ የሰብዓዊ መብት አንዱ አካል መሆኑም እርግጥ ሆኗል፡፡ ለልማት ደግሞ ወሳኝ ከሆኑት ግብዓቶች አንዱ የተፈጥሮ ሀብት ነው፡፡ የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ መጠቀም፣ ለሕዝቡ እንዲጠቅም ማድረግም ያስፈልጋል፡፡ የሕዝቡን የመልማት መብት ዕውን ለማድረግ ወይንም በራሱ መወሰኑን ለማረጋገጥ ምቹ ሕግና ፖሊሲ ማውጣት፣ እነዚህም ሲወጡ ሕዝቡን የማሳተፍና ለውሳኔ የሚሆን ሐሳብ የማበርከት መብትንም ያካትታል፡፡ ሕገ መንግሥቱ ፖሊሲዎቹና አፈጻጸማቸው ላይ ብዙ አጠያያቂ ጉዳዮች በመኖራቸው ከውጭና ከአገር ውስጥ ምሁራን የሰሉ ትችቶች በተጨማሪም ሕዝብም ቅሬታ ሲያሰማ ቆይተዋል፡፡ ትችቶቹ በዋናነት የሚያጠነጥኑት የመሬት ባልተቤትንና የተፈጥሮ ሀብትን በተመለከተና በልማት ጉዳዮች ላይ ቀድሞ ሕዝብን ያለማማከርና ያለማወያየት እንደሆነ ይታወቃል፡፡