});

በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች በካንሰር ይያዛሉበኢትዮጵያ በየአመቱ ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች በተለያዩ የካንሰር አይነቶች ይያዛሉ።

ከእነዚህም መካከል ከ44 ሺህ የሚበልጡት በበሽታው ምክንያት ህይወታቸው ያልፋል ብሏል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር።

በመሆኑም የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ በሽታውን ለመከላከል የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ጥረት ይጠይቃል ነው ያለው ሚኒስቴሩ። በአዲስ አበባ የሚካሄደውን 10ኛው አለም አቀፍ የካንሰር ጉባኤ አስመልክቶ ለሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ የሥራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

አለም አቀፍ ጉባኤው “የማህፀን ጫፍ፣ የጡትና የፕሮስቴት ካንሰርን ከአፍሪካ እናጥፋ” በሚል መሪ ሃሳብ ከሐምሌ 17 እስከ 20 ቀን 2008 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን፥ ከ500 በላይ አለም አቀፋዊና ከ2 ሺህ 500 በላይ የሀገር ውስጥ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙት ይጠበቃል፡፡

ጉባኤውን የኢፌዴሪ ቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ከፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እንደሚያዘጋጁት የሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።