});

ለኢትዮጵያ አጣዳፊ የምግብ አቅርቦት የሚበቃ እርዳታ አልተገኘምበአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ለሚቀርብላቸው 10.2 ሚሊዮን ዜጎች ከሚያስፈልገው የምግብ መጠን እስካሁን የተገኘው 54 ከመቶ ብቻ መሆኑ ታወቀ፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ለሚቀርብላቸው 10.2 ሚሊዮን ዜጎች ከሚያስፈልገው የምግብ መጠን እስካሁን የተገኘው 54 ከመቶ ብቻ መሆኑን የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አስታውቀዋል።

ኮሚሽነሩ ምትኩ ካሳ እንዳሉት ገንዘቡ የሚያስፈልገው እስከ የፊታችን ታህሣሥ ወር የእርዳታ አቅርቦትን ለመቀጠል ነው። ይሁን እንጂ እየተካሄደ ባለው የበልግ ግምገማ የተረጂዎቹ ቁጥር እና የገንዘቡ መጠን ሊከለስ እንደሚችል ጠቁመዋል።2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ የድርቅ ዓመት ማለፉና ተፅእኖውም እንደቀጠለ እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡

ያለፈው ዓመት የበልግ ዝናብ በታሰበው መንገድ አልጣለም። በዚሁ ዓመት የተጠበቀው የክረምት ዝናብም በአብዛኞቹ የሃገሪቱ አከባቢዎች ቀርቷል፡፡ እናም በያዝነው ዓመት ሊሰበሰብ የነበረው ምርት በአብዛኛው አልተገኘም። በተለምዶ የምርት መሰብሰብያና የጥጋብ ወቅቶች የሚባሉት ታኅሣሥ እና ጥር የእርዳታ መጠየቅያ ጊዜ ሲሆኑ መንግሥትና አጋሮቹ በዚሁ የታህሣሥ 2008 መጀመሪያ ይፋ ባደረጉት የሰብአዊ ድጋፍ መጠየቅያ ሰነድ 10.2 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀዋል።