});

የአንድሮይድ ስልኮች የሰዎችን የግል መረጃዎችን አደጋ ላይ እንደሚጥሉ ተመለከተበመላው ዓለም በስፋት በጥቅም ላይ የዋሉ የአንድሮይድ ስልኮች በሚስጥር የሰው ልጆችን የግል ህይወት የተመለከቱ መረጃዎችን ያለፈቃድ የማስተላላፍ ክፍተት እንዳለባቸው አንድ ጥናት ጠቆመ ።

የአንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚ የሆነ አንድ ግለሰብ ምንም ሳያውቅ የትቦታ እንደሚገኝ ፣ የሚያደርገውን የስልክ ልውውጡን በተመለከተና ሌሎች የግል ሚስጥሮቹን ለማወቅ በሚያስችል ሁኔታ በሌላ ግለሰብ መረጃዎቹ ሊበረበርበት እንደሚችል ጥናቱ አሳይቷል ።

በአንድሮይድ ስልክ ላይ የተጫኑ አፕሊኬሽኖች ፣ ድምጾችናሌሎች መጠቀሚያ ሶፍትዌሮች ሚስጥሮች አደጋ ላይ እንዲወድቁ ሁነታዎችን የሚፈጥሩ መሆናቸው ተገልጿል ።

ከአንድ መቶ በላይ በሚሆኑ የጎግል አፕሊኬሽኖች ላይ በተካሄደው ጥናት እንደታወቀው የስልክ ተጠቃሚዎች አፕሊኬሽኖችን አውርደው በሚጠቀሙበት ወቅት ከተጠቃሚው ፍቃድ ውጪ መረጃዎችን የመውሰድ ሁነታ ይታይባቸዋል ።

እንደ ማልዌር የመሳሰሉ አፕሊኬሽኖች ከአንዱ ስል ወደሌላው በሚላኩበት ጊዜ የተቀባዩን ቁልፍ መረጃዎች በመበርበር ለሚፈለገው ዓለማ ማዋል እንደሚቻል ጥናቱ አመልክቷል ።

በጎልግል ጥቅም ላይ ከወዋሉት 100ሺ የሚሆኑ ታዋቂ አፕሊኬሽኖች ውስጥ የጥናት ቡድኑ እንዳረጋገጠው 23ሺ 495 መረጃዎችን መበርበር የሚያስችሉ ጥንድ አፕሌኬሽኖች መሆናቸው ተጠቁሟል ።

አፕሊኬሽኖቹን የተኛውም ተጠቃሚ ካወረደ በኋላ የግል መረጃ ያለምንም ፈቃድ የግል መረጃን ለመበርበር ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራሉ ።

የጥናቱ ተንታኞች እንደሚናገሩት በአንድሮይድ ስልኮች ላይ የሚጫኑት አፕሊኬሽኖች እርስ በራሳቸው የሚናበቡና መረጃም የሚነግዱ መሆኑ ጥናቱ በጉልህ አሳይቷል ።


Recent Posts

See All

ከስራ በሁዋላ አየሁዋት ሄድኩና

ኢትዮጵያ ውስጥ ስራ እንዲከበር ያደረገ ደርግ ነው፤ ከዛ በፊት ስራ የተናቀ ተግባር ነበር፤ “ዋይ ዋይ ባላባት እንግዲህ ቀረ ሳይሰሩ መብላት “ ይሉ ነበር የዩኒቨርስቲ ፋኖዎች! ደርግ ስራን አስከበረ፤ አንዳንዶች እንደውም ባንድ ጊዜ ሁለት ስራ ደርበው እሚሰሩ ነበሩ ! ለምሳሌ አትሌት ምሩፅ ይፍጠር ሩጫ ልምምድ ሲ